=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እንደሚታወቀው ጋብቻ አሏህ ለሰው ልጅ ከሰጠው ኒእማዎች መካከል አንዱ ነው። ትዳር የሰው ልጅ ከመጀመሪያው ሲፈጠር በትዳር የተረጋጋና ደስተኛ ሂወትን ይመራበት ዘንድ አሏህ ያስቀመጠው የስነ-ፍጥረት ህግጋት ሲሆን ኢስላም እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ማህበረሰብ ባጠቃላይ የሰው ልጅ የትዳርን ጥቅም እንዲያገኙ ሁሌም ወደ ትዳር አለም ጥሪ ያደርጋል። ትዳር የሂወትታችን ወሳኝ ክፍል ሲሆን በኢስላም ልዩ ስፋራ ያለው የኢማናችን ግማሽ ነው።
Δ ኢማንን ሙሉ ያደርጋል
Δ ደስተኛና ፅኑ የቤተሰብ ፍቅር መስርቶ ለመኖር ያስችላል
Δ የማህበራዊ ሂወት ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል
Δ ፍቅርንና አጋርነትን ያስገኛል
Δ የሰው ልጅ የዘር ሃረግ እንዳይቇረጥ ልዩ ሚና ይጫወታል
Δ የአሏህን ውዴታ ያስገኛል
Δ የአሏህ ባሪያ ፣ ሷሊህ የሆኑና ኢስላምን የሚያገለግሉ ልጆችን በኢስላማዊ አደብ ኮትኩቶ ለማሳደግ ይረዳል
Δ የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ኡመት ከሌሎች ነብያቶች ኡመት በላይ ከፍ ያደርጋል
Δ ከሃራም ነገር ይጠብቃል
Δ የአሏህን ህግጋት ከመጣስ ያድናል
Δ ዘርን ያስገኛል
Δ የአእምሮ ሰላምን ፣ ደስታና ምቾትን ያጐናፅፋል
Δ ቀልብ የሰከነች እንድትሆን ሲያደርግ ወደ ስኬትም ያመራል
Δ ከሸይጧን ተንኮል ይጠብቃል
Δ ቀላል የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖረን ያደርጋል
♥Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ♥
© By Nejwa Bint Islam member of Youth-Mission at
Websites:
http://youth-mission.mobie.in
http://youth-mission.blogspot.com
http://facebook.com/youth.mission29
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|